ይህ ጥያቄ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በተከታይ ለሆናችሁ በተለይም በሰንበት ት/ት ቤት ላደጋችሁ ይሁንልኝ። ጥያቄዬ የሰንበት ት/ቤት መተዳደሪያ የተለያዩ አማራጭዎች አሉ ለምሳሌ በዓላት በመጡ ቁጥር በአጥቢያቸው የገቢ ማሰባሰቢያን በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ ጥሪ ማለትም ቡሄ መስቀል እንቁጣጣሽ በምዕመኑ ቤት በማድረግ ናቸው። ነገር ግን የግቢ ጉባዔ መተዳደሪያስ ምንድነው ???? እነዚህን የሰንበት ት/ት ቤቱን ስራዎች መስራት ይችላል ማለት ያለ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ፍቃድ እና ይሄንን ቢሰራስ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ኪሳራ አይዳግድም ። ሚተዳደርበት ገቢ ማሰባሰቢያ እንደ ምሳሌም ብጠቅሱልኝ። ሌላ ሰንበት ት/ቤቱ ይሄንን ስራ እንዳይሰራስ ማገድ ይችላል??? ወይ ግቢ ጉባዔውን ሚያሳግደው ህግ አለ??(ቃለ-አዋዲ) ይህ ለአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናት ብቻ ነው የጠየኩት
Sep 06, 2021ብዙ ጊዜ የግቢ ጉባኤ ቋሚ መተዳደሪያ ከሆኑት የተወሰኑት የትሪ ዕጣ፣ የአባላት መዋጮ፣ እና በጾም ሰዓት ደሞ ጠዋት ከሚሰበሰብ የተማሪዎች ዳቦን በመሸጥ ነው። የሰንበት ት/ት interference ከሌለበት ደሞ የንዋያተ ቅድሳት መሸጫ በመክፈት እና የመሳሰሉት ነው። ግቢ ጉባኤም/ማኅበረ ቅዱሳን በመዋቅር በሰንበት ት/ት ሥር እንደመሆኑ ሰንበት ት/ቱ እገዳ መጣል ይችላል።
Sep 06, 2021