ሰላም ትምህርት መቼ እንደሚጀምር የታወቀ ነገር አለ? የፈረቃውስ ጉዳይ ፀደቀ? አመሰግናለሁ
Sep 06, 2021Tekemt 1
Sep 21, 2021ሰላም ትምህርት መቼ እንደሚጀምር የታወቀ ነገር አለ? የፈረቃውስ ጉዳይ ፀደቀ? አመሰግናለሁ
Sep 06, 2021Tekemt 1
Sep 21, 2021#MoE የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረግው መረጃ የ2014 ዓ.ም የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ውይይት ሊካሄድ መሆኑን አሳውቋል:: ሚኒስቴሩ በ2014 ዓ.ም በሚኖረው የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እቀመጣለሁ ነው ያለው:: በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ አስታውሳል:: በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል መዘጋጀቱን ገልጸዋል:: በቀጣይ የሚኖረው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት ወደ ፊት ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ የሚወጣለትና ለህዝብ የሚገለፅ ይሆናል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል:: ከቀናት በፊት 'አዲስ ማለዳ ጋዜጣ' ትምህርት ሚንስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ፅሁፍ ሚኒስቴሩ የ2014 ትምህርት አሰጣጥ ከዚህ በፊት ወደነበረበት ለመመለስ ማቀዱን ገልጾ ነበር: ዛሬ ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው ፅሁፍ ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም : የ2014 ትምህርት አሰጣጥ እንዴት ይሁን የሚለውን ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሬ ወደፊት ገልጻለሁ ሲል ነው የጠቆመው:: @tikvahethiopia
Sep 06, 2021awo timiet meskerem 7 yegemeral fereka degmo yelem meselen
Sep 07, 2021በፈረቃ ሲሰጥ የነበረው የትምህርት ሒደት ወደ መደበኛው እንደሚመለስ ተገለጸ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በፈረቃ ሲሰጥ የቆየው ትምህርት በ2014 የትምህርት ዘመን ወደ መደበኛው እንደሚመለስ ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡ የኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲረዳ በማሰብ በ2013 የትምህርት ዘመን ላይ በፈረቃ ሲሰጥ የነበረው ትምህርት እና ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው የቀናት ቁጥር በሳምንት ወደ ሦስት ቀን ተቀንሶ ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ተምረው ያሳለፉ ሲሆን፣ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ነበረበት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ የትምህርት ጊዜውን ለመመለስ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ከተማ ቀውይ ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፡አዲስ ማለዳ @Free_Education_Ethiopia Stay Safe!
Sep 06, 2021