እንዴት ናችሁ ቤተሰብ አንድ በጣም ያስጨነቀኝን ነገር ላማክራችሁ ታላቅ እህቴ በቅርቡ ነው የወለደችው እናም አንዳንድ ነገር ለማገዝ ብዬ መጣሁ:: እና ባለቤቱዋ ሌሊት ሌሊት የተኛሁበት ክፍል ተደብቆ ይገባና አጠገቤ ተቀምጦ ለረጅም ሰአት ያየኛል:: እንቅልፍ የወሰደኝ አስመስዬ ዝም እላለሁ :: በዚህ ምክንያት ካሁን አሁን የሆነ ነገር እንዳያደርገኝ ስለምፈራ ሳልተኛ እንዲሁ ፈጥጬ ነው የማድረው ከዚህ በፊት እህቴ ከቤቱ ሰራተኝ ጋ አግኝታው በስንት ሽምግልና ነው የታረቁት በዚህ ምክንያት ሰራተኛ መቅጠር ተወች:: በጣም ፈርቻለሁ ወደ ቤቴ እንዳልመለስ አራስ እህቴን ማን ያግዛታል እንዳልነግራት ደግሞ በጣም ከባድ ረብሻ ይነሳል እስኪ መፍትሄ የምትሉትን ንገሩኝ::
Sep 04, 2021if there is a door, lock the door when you sleep. or create a reason sleep beside your sister.
Sep 05, 2021