አዳም'ና ሄዋን በሰይጣን ምክንያት እፀ በለስ በልተው ከገነት ባይባረሩ ኖሮ፥ እናንተም ይሄን ፁፍ አታነቡትም፤ እኔም አልፅፈውም ነበር። ምክንያቱም፥ ገነት ውስጥ ወሲብ የለም። መፅሀፉም ቢሆን አዳም'ና ሄዋን ከገነት ከወጡ በኋላ፥ “አዳምም ሚስቱን ሔዋንን ዐወቀ (ወሰበ)፣ ፀነሰችም፤ ቃየንንም ወለደች።” (ዘፍ ፬፥፩) ይላል። በወንጌል ደግሞ “…በሰማያት (በገነት) እንደ እግዚአብሄር መላእክት ሆነው ይኖራሉ እንጅ አያገቡም፤ አይጋቡምም።” (ማቴ ፳፪፥፴) እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ገነት ውስጥ ወሲብ እንደሌለ ይገልፃሉ። …ያለወሲብ ደግሞ የሰው ልጅ መራባት እንደማይችል ማስረዳት አይጠበቅብኝም። ለሰይጣን ክብር ይግባው'ና 😂 ሄዋንን አስቶ (እንደብዙዎቹ እሳቤ ዋሽቶ) እፀበለስን አስበላት፤ እግዜሩም አዳምን ከሄዋን ጋር ከገነት አስወጣቸው፤ አይኖቻቸው ተገለጦ ነበርና እስር በርሳቸው ተቃቀፉ፤ የወሲብን ጥፍጥናን ቀመሱ፤ እኛም በወሲብ መጨረሻ በስሜት መጀመሪያ ላይ በሚከፈል ግብር፣ ግዙፍ ነስተን ህያው ሆንን። ካለመኖር ወደ መኖር ተሸጋገርን። ሰይጣን ልንኖር ያልነበርን ሰወችን ህልው ሲያደርግ፣ እግዜር ደግሞ በንፍር ውሀ ሰወችን አጥፍቷል። …በዚህ መካከል ማን ነው ቅዱስ? ሰይጣን ወይስ እግዜር?
Aug 31, 2021የ እዉቀትህን ልህቀት እንመልከት በመጀመርያ ገነቱስት ወሲብ እንደሌለ የሚያሳይ ነገር የለም በሰማይ ነዉ ወሲብ እንደሌለ እሚያወራዉ በ ዳግማዊ መፅአት ነዉ በዛ ደሞ ሰማይም ምድርም ጠፍቶ አዲስ ሰማይ እና ምድር እንጂ ገነት አይደለም ሲቀጥል አሁን ሰዉ ቢሞት ገነት እሚገባዉም በነፍስ ነዉ በስጋ አይደለም በነፍስ ደሞ ተራክቦ የለም ስለ ቅድስና እዉቀት ይቀርሀል በጣም ከመደነዝ የተነሳ ብቻ ተወዉ
Sep 01, 2021