For those who are Orthodox, bete Christian and ken snmar gelan be senbet ken metateb hatiat new teblenal ena yemitawku kehone lemn endehone btnegrugn Amesegnalehu😀
Aug 30, 2021በፍጹም እንዲህ የሚል አስተምህሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን የላትም።ይሄ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ በልማድ በዚሀ ቀን እንዲህ ይደረጋል በዚያ ቀን እንዲህ አይደረግም ይላሉ ነገርግን ይሄ ትክክል አደለም።እሁድ ሰንበት የጌታ በዓል ስለሆነች ከሥጋዊ ስራ አርፈን በመንፈሳዊ አምልኮ እንድናሳልፍ ግድ ይላል።ሰንበትን ማክበር አምላካዊ ትዕዛዝ ስለሆነ(ዘጸ20፥8)።ነገር ግን እንደ ግብዞች አይሁዳውያን እና ፈሪሳውያን ካጠፉ ማይዘረጉ ከዘረጉ የማያጥፉ ሰንበትን ቁጭ ብሎ መዋል ተገቢ አይደለም።በጸሎት፣በምጽዋት መትጋት ያስፈልጋል።እና ቀላል ስራ መስራትም አያስነቅፍም የታመመን መርዳት፣ምግብ ማብሰል፣ሰውነትን መታጠብ፣የሞተን መቅበር በሐዲስ ኪዳን ሰንበትን እንዳለማክበር አያስቆጥርም።
Aug 30, 2021