Passport online endet new mimolaew pls aza aregegn eko
Aug 29, 2021#REPOST አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት ምን ያስፈልገኛል ? አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት አመልካቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ 1. ይህን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሰነዶች ማዘጋጀት ፦ • ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ • የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት/ማስረጃ 2. የሚያመለክቱት ለአስቸኳይ አገልግሎቶች ከሆነ ከሚከተሉት መካከል ቢያንስ አንዱ ሊኖርዎት ይገባል ፦ • የሕክምና ደብዳቤ • የትምህርት እድል እና ዲቪ • ከተፈቀደለት ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ • የውጭ ሀገር የነዋሪነት ፍቃድ • የግብዣ ደብዳቤ • አስቸኳይ የስራ ጉዞ • በሀዘን/ጋብቻ ምክንያት የሚደረግ ጉዞ 3. ለአዲስ ፓስፖርት የሚከፈለውን ክፍያ ያረጋግጡ ፦ • ለ32 ገጽ ፓስፖርት - 600 • ለ64 ገጽ ፓስፖርት - 2186 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍላችሁ online አድራሻ ላይ አባሪ ያደርጉታል። ኦንላይ ላይ "ለአዲስ ፖስፖርት" አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎት ለማግኘት ይህን ሊንክ ተጠቁሙ👇 www.ethiopianpassportservices.gov.et @TIKVAHETHIOPIA
Aug 29, 2021