ፍቅረኛዬ ከዚህ በፊት ማንም ቢያናግራት የፈለገችውን ብታደረግ ምንም ግድ አይሰጠኝም ነበር (ምንም እንደማታደረግ አውቃለሁ ግን ብታደርግም ምንም አይመስለኝም ነበር ) እሷን አናገርኳት አላናገርኳት ምንም አይመስለኝም ነበረ እሷን የማግኘት ፍላጎትም ብዙም አልነበረኝም:: አሁን ላይ በጣም ግራ ሚያጋባኝ ነገር እየተፈጠረ ነው በቃ ቀኑን ሙሉ እሷን ነው ሳስብ የምውለው በ ትንሽ ነገር ነው ምናደድባት ወንድ አጠገቧ ካየሁ በቃ ማረገውን ነው ማጣው እና ግራ ገብቶኛል:: እንደምትወደኝ አውቃለሁ ግን በቃ በትንሽ በ ትልቁ መቅናት ጀምሪያለሁ ከዚህ በፊት ለሷ የለለኝ ነገር ነው እየተሰማኝ ያለው አእምሮየም እረፍት ማግኘት አልቻለም እና ምን ባደርግ ይሻለኛል?
Aug 24, 2021መጀመሪያው ነበር ሊገርምህ የሚገባው ጃል ... እንዴት ፍቅረኛህ ሆና ግድ አይሰጠኝም ትላለህ ሆ ስንት አይነት ሰው አለ ባካችሁ ለማንኛውም አዲስ የምትለው ስሜት ነው እንዳፈቀርካት የሚመሰክረው በልክ አድርገው የምን ከጥግ ወደ ጥግ መዝለል ነው መሀሉን ተጠቀምበት እስኪ
Aug 25, 2021