Hellow,ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ስለገባኝ ነው።...ነገሩ ወዲህ ነው ከፍቅረኛዬ ጋር የተዋወቅነው ግቢ ፍሬሽ ማን እያለን ነው ከዛም አመቱ መጨረሻ ላይ ፍቅር ጀመርን ታዲያ ከግቢ እስክንወጣ በጣም ደስ የሚል ፍቅር ነበረን እናም ስራ ስንጀምርም አንድ ቦታ ተቀጠርን ስራ ከጀመርን በሁዋላ አዳዲስ ጓደኞች አፈራች ለነገሩ ለኔም ለሷም የስራ ባልደቦች ስለነበሩ ጓደኝነታቸው አይረብሸኝም ነበር በዚህ መሀል ግን part time የምሠራው ስራ Busy ሆንኩኝ። እሷም ከጓደኞቿ ጋር እና ከአንዱ ጋር የነበራት ነገር ይረብሸኝ ጀመር እናም መጠራጠር ጀመርኩ ሳጣራም ሁለቱ Over እንደሚወጡ ደረስኩበት ..ሌላም ሌላም አንድ ቀን ቤት ነኝ ብላ እሱ ቤትም ሆና አግኝቻታለሁ በዛም በጣም ተጣለን እሱ ቤት መሆኗን ሳላቅ በፊትም አወርተን እሷም ለሱ ሌላ ስሜት እንዳላት ነግራን ይቅታ እንደረግላት ጠየቀችኝ እኔም አደረኩላት ነገር ግን ከውስጤ ሊጠፋ አልቻለም ሙሉ በሙሉ ለእሷ ያለኝ እምነት ሞተ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ደስተኛ አይለሁም ኋላ ከ3 ዓመት በሁዋላ ሁለት አመት በስራ ምክንያት ተራርቀን ኖርን በዚህ መሀል እኔ ደሞ ለእሷ ያለኝ ነገር ቀነሰ በዛ መሀልም ሌላ ሰው ተዋወኩኝ ወደድኳትም አሁን ተመልሳ መታለች አሁን ላይ ምንም ስሜት የለኝም እና ግን መናገር አልቻልኩም በዛ ላይ family involve አድርጓል እና በጣም ጨንቆኛል በዚህ ከቀጠልኩ አብዳለሁ ምን ይሻለኛል?
Aug 23, 2021መጀመሪያ የሚሻላትን መርጣለች አንተ ላላቺሁ ነገር ስትታመን እሷ ግን ያንተ ተቃራኒ ነበረች ጊዜ ስላልሰጠሀኝ ሊሆን ይችል ይሆናል ምክንያቷ ግን እ ንደዛም ቢሆን ፊት ለ ፊት ልትነግርህ ይገባ ነበር ብቻ እውነቱን ተናግሮ በመሸበት ማደር የሚባል ነገር አለ ልብህ ያላመነበትን ምንም ነገር አታድርግ her ቤተሰብ involve ቢያደርግም ይሄ ሂዎት ነው ዛሬ ለሰው ብለህ ያደረከው ነገ ላይ ሂዎትህን ያበላሻል የእኔ እይታ እንደዚህ ነው ብቻ ሰዎችንም በደንብ አዋራ ቸኩለህ አትወስን
Aug 24, 2021