🍭ፍሬሽ ማን ነኝ እና እንዴት እንደምጣጠኑ ንገሩኝ እስኪ (study tips, styles)
Aug 23, 2021በመጀመርያ የHighschool እና የጊቢ አጠናን ይለያያሉ። ጊቤ ላይ ጥሩ ግሬድ ይዘኽ ለመውጣት የኮርሱን "Exam Portion" ማወቅ በቂ ነው። ለምሳሌ እኔ በተማርኩበት ጊቢ "Exams" ላይ ሁሌ ባይሆንም የአምና፣ የካቻምና ፈተናዎች ይደጋገማሉ፤ Even ቁጥር ሳይቀየር! ይደጋገማል ስልህ ደግሞ😅 "Completely" አታጥና ማለቴ አይደለም። ወጥረህ እያጠናክ "Exams"፣ "Worksheets"፣ "Assignments" ስራ! መምህሩ ሲያስተምር #ኖት የወሰድክበት ደብተር በመጀመርያ ቀርጥፈህ አንብበው፣ ተረዳው። እሱን ስትጨርስ ወደ ሌላ ክላስ በሌላ አስተማሪ የተማሩትን ደብተር አጥና። ይሄን ስተጨርስ "Handout or soft copy" አንብብ! ጊዜ ሲኖርክ ደግሞ "Course Outline" ላይ ያሉትን "Reference Books" ፈተና ይመጣባችኋል የተባለው ቦታ ላይ ሄደህ አንብብ! ላይብረሪ የምትጠቀም ከሆነ ትልቅቅ መጽሐፍትን ደብተርህን አንብበህ ሳትጨርስ እንዳታነባቸው። ያልገባህ ነገር ካለ ሰው ጠይቅ! መረዳዳት አንዱ የጊቢ የግሬድ ስኬት ነው! ጊቢ ላይ ቡልጥ መሆን ነው የሚያዋጣው፤ በፈተና መዳረሻ ሰአት አትጨነቅ። ምንም የተለየ ነገር የለም ካጠናኽው ውጪ!
Aug 23, 2021