በጣም የምወዳት ልጅ አለች እና እስካሁን ድረስ እንደምወዳት አልነገርኳትም ግን ጓደኛማቾች ነን እንቀራረባለን 1ኛ ክፍል ስገባ ነው የተዋወኳት እና እሁን 12ኛ ክፍል ነን አሁንም ድረስ አንድ ክፍል ውስጥ ነው ምንማረው....ልጅቷ ደሞ በጣም ጨዋ ናት አስከዛሬ ድረስ ፍቅረኛ የሚባል ነገር የላትም...እና ዛሬ በህልሜ ሞታ አየኋት የእውነት መስሎኝ በጣም ደንግጬ ነበር በቃ መቅብሯ ላይ ሄጄ እንደምወዳት ልነግራት እያሰብኩ ከእንቅልፌ ባነንኩ ሰአቱ ከለሊቱ 8:20 አካባቢ ይሆናል... እባካችሁ በምታውቁት ጎበዝ ህልም ፈቺ አስፈቱልኝ።
Aug 22, 2021ሞት ብዙ ትርጉም አለው።በህልም ሲታይ ለምሳሌ ጥጋብ ነው።ያው በዚህ ግን ምናልባት ቀን ቀን ስጋት ውስጥ ነህ፡ትምህርት ጨርሳችሁ የተለያየ ግቢ ስትገቡ፥ወይ እሷ ወደ ሌላ ቦታ ትሄድ ይሆን የሚል ስጋት ካለብህ እንድትግራት መወሰን እንዳለብህ ለማሳየት እንደመመልክት ይሆናል።ጊዜው ሳይረፍድ ማለት ነው። አዲስ ነገር ተፈጥሮ፡ከሆነ፡ሜሴጅ ብታረግልኝ።
Aug 22, 2021