እባካቹ እርዱኝ ከህሊና ፀፀት ላመልጥ አልቻልኩም ተማሪ ነርስ ነኝ ከቀናት በፊት ድንገተኛ ክፍል የነበረ ታማሚ ወደኔ እንዲዘዋወር ተደርጎ ስከታተለው ነበር በርግጥ ህመሙ ከባድ ነበርና ለህይወቱ ስለሚያሰጋው ከፍተኛ ክትትል ውስጥ ነበር ታዲያ በእለቱ Deamolactocine የተባለ የመዳኒት መስጠት ሲገባኝ በስህተት የማንቂያ መርፌ ሰጠሁት በርግጥ የሰጠሁት መርፌ ጉዳት አልነበረውም ግን መስጠት የነበረብኝን መዳኒት ባለመስጠቴ ህይወቱ አልፋለች ደክሞ ስለነበር በተፈጥሮ ሞት የሞ መስሏቸው ያለምንም ጥያቄ ልባቸው ተሰብሮ አዝነው ወስደውታል እኔ ግን አልቻልኩም ምናልባት ብናገር በቀላሉ ስራ ከማጣት ጀምሮ እስከ ከባድ እስር ይጠብቀኛል ዝም ማለቱም ከበደኝ ምን ላድርግ
Aug 20, 2021ስለታሰርክ ከ ፀፀት ትድናለህ ማለት አደለም ፈጣሪህን ይቅር እንዲልህ ተማፀን በእርግጥ ከባድ ነው ግን ሌላ አማራጭ የለህም እንደውም ስራው ውስጥ ሆነህ ከዚ ቡሀላ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ምትችለውን እያረክ ሰዎችን ከሞት በማዳን ስህተትህን ማካካስ ትችላለህ አይዞን
Aug 20, 2021