በህፃንነቴ አያቴ የዘመድ ልጅ ከገጠር አምጥታ ታሳድግ ነበር ያኔ እኔ በጣም ህፃን ነበርኩ ልጅቷ እኔን 2 አመት ትበልጠኛለች አባቴ እሷ ከመጣች ጀምሮ እኔ እና ወንድሜን ሙሉ ለሙሉ እረስቶናል በፊት ህፃን ስለነበርኩ ብዙም አይሰማኝም ነበር አሁን ግን በጣም መናደድ ጀመርኩ እሱ ሰላም ሲል እራሱ እሷን ብቻ ነው እኔ የምማርበት ትምህርት ቤት እግሩ አይረግጥም እሷ ጋር ግን ሁሌም ነው የሚሄደው በአጠቃላይ ለእኔ እና ለወንድሜ ሁሉንም ነገር የምታደርገው እናቴ ናት በምዕንም አይረዳትም የሚያመጣውን ገንዘብ ለእሷ ልብስ እና ጫማ ይገዛበታል አሁን በእሱ ምክንያት ከልጅቷ ጋር ያለኝ ግንኙነት እየተበላሸ ነው አንዳንዴ እሷ ባትኖር ኖሮ አባቴ ይወደኝ እንደነበር አስባለሁ ከድሮውም የአባቴን ፍቅር ለማግኘት አሞክር ነበር ልጅቷ ልክ እንደእህቴ ናት እሷን ላጣትም ሆነ ላስከፋት አልፈልግም ግን ሳላስበው በጣም እያስከፋሁዋት ነው እና ይሄንን ሳስብ ስሜቴ ድብልቅልቅ ይልብኛል በቃ ይቅር ሰው ያለ አባት መኖር ይችላል ብዬም የማስብበት ቀን አለ ብቻ ጨንቆኛል እና እሷን ሳላስከፋ የአባቴን ፍቅር የማገኝበትን ዘዴ አማክሩኝ እባካችሁ
Aug 18, 2021Have u ever taught that she would be his first born child , she might be ur real sister ,
Aug 18, 2021