#ቡሄ_በሉ ቡሄ በሉ (2) ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(2) የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(2) ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ አባቱም አለ ልጄን ስሙት ቃሌ ነውና የወለድኩት ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ በተዋህዶ ወልድ የከበረው የእግዚአብሔር አብ ልጅ ወልደማርያም ነው ቡሄ በሉ/2/ የአዳም ልጆች ብርሃንን ተቀበሉ አባቴ ቤት አለኝ ለከት እናቴ ቤት አለኝ ለከት አጎቴም ቤት አለኝ ለከት ተከምሯል እንደ ኩበት የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ ከደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ያላችሁ ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ ችቦውን አብሩት እንዳባቶቻችሁ ምስጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ አባቶቻችን ያወረሱን የቡሄን ትርጉም ያሳወቁን እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን ይህን ነውና ያስረከቡን ለድንግል ማርያም አሥራት የሆንሽ ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ በረከታቸው ያደረብሽ ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ ለሐዋርያት የላከ መንፈስ ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ በበጎ ምግባር እንድንታነጽ በቅን ልቦና በጥሩ መንፈስ በረከተ ቡሄ ለሁላችን ይድረስ ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2) እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3) 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Aug 18, 2021