Heleme lelit (ህልመ ሌሊት) aschegeregn endt laskumew Please its serious
Aug 17, 2021ሕልም፥ ራእይ፥ ሕልመ ሌሊት፥ መፍትሔው፥ እጽዋት 😇ሕልም በሰዎች ላይ የሚከሠተው በ፬ቱ[4ቱ] የሥጋ ባሕርያት መጋጨት ምክንያት እንደኾነ የሥነ-ፍጥረት መጽሐፍት ያስረዱናል። አንድም ሕልም መላእክት ከእግዚአብሔር ታዘው ለሰውልጆች የሚያስተላልፉት ራእይ ወይንም ደብዳቤ ነው ። 🌼ለምሳሌ🌼 ያኽል 🌪 የነፋስ ባሕርያችን ሲጸናበት በሕልማችን ምን እንደሚታየን እንመልከት። 💨ሰውየው በሠረገላ ሲሽከረከር፥ ሲበር፥ ግልቢያ፥ የተኛበት አልጋ ሲዞርና ይዞት ሲገለባበጥ፥ ጢያራ ሲበር፥ ሲሸሽ፥ ሲሮጥ፥ ሽሽቀዳደም እነዚኽን የመሳሰሉ ሕልሞችን ሰውየው ይመለከታል። 😳አጋጥሟችኹ ያውቃል ? 👉ሕልም ከነዚኽ ከ፬ ባሕርያተ ሥጋ አለመስማማት የተነሳ የሚከሰት ነውና ደስ የሚል ሕልም ስናይ በከንቱ እንዳንደሰትና የሚያስደነግጥ ሲኾን ደግሞ እንዳንሰጋ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ❓ሕልመ ዮሴፍ{ራእይ}ና የባሕርያት መጋጨት የኾኑትን ሕልሞች በምን እንለያቸው ? ሕልመ ዮሴፍ ወይንም ራእይ ከሆነ ሕልሙ/ራእዩ ለተደጋጋሚ ቀናት የሚታየን ይኾናል። አንድም ቶሎ ብሎ እውን ይኾናል:: የባሕርያት መጋጨቶች ግን በተደጋጋሚ ቀናት የሚታዩ አይደሉም። ❓ሕልመ ሌሊትስ በ፬ቱ መጋጨት የሚመጣ ነው ? አይደለም። ወንድ ሕልመ ሌሊት የሚታየው ሴት ዓይነጥላ ካለበት ነው ፤ ሴት ሕልመ ሌሊት የሚታያት ወንድ ዓይነጥላ ካለባት ነው። ዓይነ ጥላዎቹ በኹለቱም ጾታዎች ላይ በሕልማቸው ዝሙታዊ ተግባርን ያሳዩኣቸዋል። ሕልመ ሌሊት ያጋጠማቸው ሰዎች ጸሎት እንዲተውና ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይሄዱ የመንፈሳዊነት ዝቅጠት እንዲያጋጥማቸው ዓይነጥላዎቹ 24 ሰዓት ይታትራሉ። ታዲያ በጾም በጸሎት በስግደት ካልታተርን በቀር ዓይነጥላዎቹ በእየዕለቱ ቋሚ የወሲብ ጓደኛ ሊያደርጉን ይችላል፥በዚኽ ክስተት ውስጥ ያለ ሰውን ዓይነ ጥላዎቹ ከጋብቻ በኋላም ቢኾን እንደማይለቋቸው ይነገራል ። ⚠️ሕልመ ሌሊት ካጋጠመን በዚያው ቀን ይዋል ይደር ሳንል በመጸጸት ልናነባና ይቅርታን ልንጠይቅ ይገባል ። 🔆መፍትሔው፦🔆 👇👇👇 ከሕልመ ሌሊትና ከቅዠት መዳኛ ጥበቦች ብዙ ጥበቦች አሉ ጥቂቶቹንና ቀለል ያሉትን የምነግራችኹ ይኾናል በደንብ አንብቡት ። 👇 1⃣ መዝሙረ ዳዊት ፦ 💠መዝሙር ፲፩{11} ን 7 ጊዜ ደግመኽ/ሽ ብትተኛ/ተኚ ከክፉ ሰውና ከቅዠት ሕልም ትድናለኽ/ኛለሽ። 💠መዝሙር ፴{30} ን በልሙጥ ወረቀት ጽፈኽ/ሽ ብትይዘው/ዢው ሌሊት አትባንንም/ኝም። 💠መዝሙር ፵፪{42} ን ጽፈኽ/ሽ ብትይዘው/ዢው ከሌሊት ፍርሃት፥ ከመባነን፥ ከቅዠት እድናለኽ/ሽ። 💠መዝሙር ፺፯{97} ን በልሙጥ ወረቀት ጽፈህ/ሽ 7 ጊዜ ደግመኽ/ሽ ዕጣን ታጥነኽ/ሽ ብትይዘው/ዢው ዘወትር በክፉ ህልም ከመቃዠት ያድናል። 2⃣ 🌳 እጽዋት 🌴፦ የሎል ቅርፊት ወደ ምሥራቅ በኩል ቀርፈህ ማታ እሳት ላይ አድርገኽ/ሽ ታጥነኽ/ሽ ተኛ/ኝ ከመኝታኽ ስትነሳ ያደረ ሽንትህን ብትሸና ይለቃል። 🤔 ሌላም በእጽዋት ዙሪያ አሉ ነገር ግን ላታገኙ ስለምትችሉ፥ መዝሙረ ዳዊትን እንድትሞክሩ አሳስባለኹ። 🔆ሕልመ ዮሴፍ፥ ራእይ ለማየት😇 ✡መዝሙረ ዳዊት ፦✡ 💠መዝሙር ፴፮{36} ን ክፉም ኾነ በጎ በራእይ ለማየት 7 ጊዜ ደግመኽ/ሽ ተኛ/ኝ። 💠መዝሙር ፴፰{38} ን 7 ጊዜ ደግመኽ/ሽ "እግዚአብሔርን ስለ ድንግል ማርያም ስለ እመብርሃን ተማጽኘሃለኹ የፈለኩትን አሳየኝ" ብለኽ/ሽ ብትተኛ/ኝ ያሳይሃል/ሻል። ፍቱን ውእቱ it is tasted. 💠መዝሙር ፸፰{78} ን ደግመኽ/ሽ ስትተኛ/ኝ ያሰብከውን/ሽውን ነገር ሁሉ ራሱ መዝሙረኛው ዳዊት መጥቶ ይነግርሃል/ሻል። 😳
Aug 18, 2021