Can the Atheist out here explain what ቡዳ is
Apr 20, 2020በቀዳሚነት ቡዳ አለ ብለው የሚያምኑ የጥንታዊ ግሪክና የሮማ ሰዎች እንደ ነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ቡዳ የሚበላው ወይም ሰዎችን የሚያጠቃው ብዙ የሚመሰገኑትንና ከሚገባቸው በላይ የአድናቆት ሲሳይ የሚወርድላቸውን ሰዎች ነው፤ የሚመሰገኑ ሰዎች በምስጋና ብዛት ስለሚታበዩ በገዛ ራሳቸው የቡዳን መናፍስት በመጥራት ለአካላዊና አእምሮአዊ በሽታዎች ተጋላጭ ይሆናሉ፤ ማንኛውም ምክንያቱ በውል ያልታወቀ በሽታና መጎሳቀል በቡዳ የመበላት ምልክት ነው ተብሎ ይታመን ነበር፡፡ ይህም የሚሆነው አማልክት ሰዎች ባገኙዋቸው ውጤት፤ ታዋቂነት፤ ዝነኝነት፤ መኩራራትና አድናቆት ብዛት ስለሚቆጡ እንደመቀጣጫ ሰዎችን በቡዳ መንፈስ ወይም ዓይን ይወጋሉ ተብሎ ይነገራል፡፡ የቡዳ መንፈስ ምንጩ ዓይን ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ከዓይናቸው ከፍተኛ ኃይል የሚያመነጩ ሰዎች ሲኖሩ ከዓይናቸው የሚወጣው ኃይል ሌሎች ሰዎችን እንዳይጎዳ ዘወትር መነጽር እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፡፡ በሌላ መልኩ ብዙ አድናቆትና ውዳሴ የቡዳ መንፈስን ይጠራል ተብሎ ስለሚታሰብ የሚያማምሩ ልጆች ሲወለዱ ውበታቸውን ተመልክተው ሰዎች ከተቻለ እንዳያደንቁ ይህ የማይሆን ከሆነ ከአድናቆታቸው በኋላ ምራቃቸውን የልጆች ፊት ላይ እንትፍ ብለው እንዲተፉባቸው ወይም ፈጣሪ ይባርካችሁ ማለት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ቡዳ የሚበላው ሰዎችን ብቻ ሳይሆን የሚታለቡ ላሞች ወተት እንዳይሰጡና እንዲነጥፉ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለ፡፡ በአንድ አንድ ቤተ እምነቶች አስተምህሮ መሠረት በሰዎች ህይወት ውስጥ የሚከሰቱ ትልልቅ ለውጦች ማለትም ለአቅመ አዳማና ሄዋን መድረስ፤ የሰርግና የመውለድ ወቅቶች ቡዳን የመጥራት ትልቅ ዕድል ስላላቸው በእነዚህ ወቅቶች ሰዎች ከአድናቆት፣ ራስን ከማኮፈስ፤ እንግዳ የሆኑ ሰዎችን ከማግኘት እንዲታቀቡ ይመከራሉ፡፡ በተመሳሳይ በሂንዱ እምነት መሰረት አንድ አንድ ወንዶች የቡዳ መንፈስ ቢኖርባቸውም ሴቶች የቡዳ መንፈስንና ዓይን በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሴቶች የቡዳ መንፈስ ራሳቸውንና ሌላውን እንዳይጎዱ ሲሉ ዓይናቸውን ኩል ይኳላሉ፡፡ በእርግጥ ቡዳ ምንድን ነው? በተለያየ ጊዜ በተደረጉ የሳይንስና የምርምር ውጤቶች በእርግጠኝነት የቡዳ ዓይንና መንፈስ ስለመኖሩ ማረጋጋጥ አልተቻለም፡፡ እስካሁን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ያላቸው የሃይማኖት ተቋማት ብቻ ናቸው፡፡ እምነታዊ ጉዳዮች ረቂቆች ስለሆኑ በሳይንስ መነጽር መመርመር ስለሚያስቸግር ግኝታቸውን ለማጽደቅም ሆነ ውድቅ ለማድረግ ያስቸግራል፡፡ ከማኅበራዊ ሳይንስ (Sociology) አንጻር ቡዳ በማኅበረሰቡ የተፈጠረ ማኅበራዊ ምናብ ወይም መንፈስ ነው፡፡ ሰዎች ተስማምተው ፈጠሩት ተስማምተው ለትውልድ አሻጋገሩት በማለት የዘርፉ አጥኚዎች ሀሳባቸውን ይገልጻሉ፡፡ በተሳሳተ መረጃ ሰዎች ሌሎችን ቡዳ ናቸው ብለው አድሎና መገለልን እንዳይፈጽሙባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትንም ይሰጣል፡፡ Source: www.zepsychologist.com
Apr 21, 2020