10tu tezazate 3 becha new mawekew please selemalawekw negerugn
Aug 14, 2021ኦሪት ዘጸአት Exodus 20 ምዕራፍ፡20። 1፤እግዚአብሔርም፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦ 2፤ከግብጽ፡ምድር፡ከባርነት፡ቤት፡ያወጣኹኽ፡እግዚአብሔር፡አምላክኽ፡እኔ፡ነኝ። 3፤ከእኔ፡በቀር፡ሌላዎች፡አማልክት፡አይኹኑልኽ። 4፤በላይ፡በሰማይ፡ካለው፥በታችም፡በምድር፡ካለው፥ከምድርም፡በታች፡በውሃ፡ካለው፡ነገር፡የማናቸውንም፡ም ሳሌ፥የተቀረጸውንም፡ምስል፡ለአንተ፡አታድርግ። 5፤አትስገድላቸው፥አታምልካቸውምም፤በሚጠሉኝ፡እስከ፡ሦስተኛና፡እስከ፡አራተኛ፡ትውልድ፡ድረስ፡የአባቶች ን፡ኀጢአት፡በልጆች፡ላይ፡የማመጣ፤ 6፤ለሚወዱኝ፥ትእዛዜንም፡ለሚጠብቁ፡እስከ፡ሺሕ፡ትውልድ፡ድረስ፡ምሕረትን፡የማደርግ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ አምላክኽ፡ቀናተኛ፡አምላክ፡ነኝና።ፕ፡ 7፤የእግዚአብሔርን፡የአምላክኽን፡ስም፡በከንቱ፡አትጥራ፤እግዚአብሔር፡ስሙን፡በከንቱ፡የሚጠራውን፡ከበደ ል፡አያነጻውምና። 8፤የሰንበትን፡ቀን፡ትቀድሰው፡ዘንድ፡ዐስብ። 9፤ስድስት፡ቀን፡ሥራ፡ተግባርኽንም፡ዅሉ፡አድርግ፤ 10፤ሰባተኛው፡ቀን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡ለአምላክኽ፡ሰንበት፡ነው፤አንተ፥ወንድ፡ልጅኽም፥ሴት፡ልጅኽም፥ሎ ሌኽም፥ገረድኽም፥ከብትኽም፥በደጆችኽም፡ውስጥ፡ያለ፡እንግዳ፡በርሱ፡ምንም፡ሥራ፡አትሥሩ፤ 11፤እግዚአብሔር፡በስድስት፡ቀን፡ሰማይንና፡ምድርን፥ባሕርንም፥ያለባቸውንም፡ዅሉ፡ፈጥሮ፡በሰባተኛው፡ቀን ፡ዐርፏልና፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡የሰንበትን፡ቀን፡ባርኮታል፡ቀድሶታልም። 12፤አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፤እግዚአብሔር፡አምላክኽ፡በሚሰጥኽ፡ምድር፡ዕድሜኽ፡እንዲረዝም። 13፤አትግደል። 14፤አታመንዝር። 15፤አትስረቅ። 16፤በባልንጀራኽ፡ላይ፡በሐሰት፡አትመስክር። 17፤የባልንጀራኽን፡ቤት፡አትመኝ፤የባልንጀራኽን፡ሚስት፡ ሎሌውንም፡ገረዱንም፡በሬውንም፡አህያውንም፡ከባል ንጀራኽ፡ገንዘብ፡ዅሉ፡ማናቸውንም፡አትመኝ። 18፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ነጐድጓዱንና፡መብረቁን፥የቀንደ፡መለከቱን፡ድምፅ፥ተራራውንም፡ሲጤስ፡አዩ፤ሕዝቡም፡ባዩ ፡ጊዜ፡ተርበደበዱ፥ርቀውም፡ቆሙ። 19፤ሙሴንም፦አንተ፡ተናገረን፡እኛም፡እንሰማለን፤እንዳንሞት፡ግን፡እግዚአብሔር፡አይናገረን፡አሉት። 20፤ሙሴም፡ለሕዝቡ፦እግዚአብሔር፡ሊፈትናችኹ፥ኀጢአትንም፡እንዳትሠሩ፡ርሱን፡መፍራት፡በልባችኹ፡ይኾን፡ዘ ንድ፡መጥቷልና፥አትፍሩ፡አለ። 21፤ሕዝቡም፡ርቀው፡ቆሙ፥ሙሴም፡እግዚአብሔር፡ወዳለበት፡ወደ፡ጨለማው፡ቀረበ። 22፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡አለው፦ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡በል፦እኔ፡ከሰማይ፡እንደ፡ተናገርዃችኹ፡እናን ተ፡አይታችዃል። 23፤በአጠገቤ፡ምንም፡አታድርጉ፤የብር፡አማልክት፡የወርቅም፡አማልክት፡ለእናንተ፡አታድርጉ። 24፤የጭቃ፡መሠዊያ፡ሥራልኝ፥የሚቃጠለውንና፡የደኅንነት፡መሥዋዕትኽን፡በጎችኽንም፡በሬዎችኽንም፡ሠዋበት፤ ስሜን፡በማሳስብበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ወዳንተ፡መጥቼ፡እባርክኻለኹ። 25፤የድንጋይም፡መሠዊያ፡ብታደርግልኝ፡ብረት፡በነካው፡ድንጋይ፡አትሥራው፤በመሣሪያ፡ብትነካው፡ታረክሰዋለ ኽና። 26፤ኀፍረተ፡ሥጋኽ፡በርሱ፡እንዳይገለጥ፡ወደ፡መሠዊያዬ፡በደረጃ፡አትውጣ።
Aug 17, 2021