Hi guys and tyake neberegn mn meselachu👇 Sega personally be life lay yemiyametaw gudat mndn nw
Aug 12, 2021ጠቃሚ ምክር ለሁላችሁም ሴጋ(Masturbation) እና መዘዙ (ብዙም ስለማናወራው ነገር ግን ስለምናደርገው ጎጂ ልማድ ለምክክር እንዲረዳ በግለጽ ቋንቋ የተጻፈ ነውና ምቾት የሚነሳህ መስሎ ከተሰማህ ያለማንበብ ምርጫው ያንተ ነው) ጀግናው ወንድሜ! ዛሬ ስለ ግለ-ወሲብ ከአሁን በኋላ ሴጋ እያልኩ የምጠራውን ጎጂ ልማድ በአንተ እና በትዳርህም ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ላወራህ እፈልጋለሁ። ይኽ ጎጂ ልማድ ከሚያመጣው መዘዞች ውስጥ መንፈሳዊ ጉዳቱን ሳይኾን አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ጠባይዓዊ.. ) ኪሳራውን ላወያይህ ፈልጌያለሁ። ይኼም ጽሑፍ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጽሑፎቼ ከራሴ ሕይወት የተማርኩትን በንባብም ያዳበርኩትን እውቀት ያማከለ ነው። እነኾ.... ሴጋ (በወንዱም ኾነ በሴቷ) መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የእድሜ ልክ ክፉና ጎጂ ልማድ ነው። ክፉ አልኩት ይኽ ዐመል አንዴ ከተጠናወተ(ሴቷንም ኾነ ወንዱን) ለመተው እጅግ ከባድ ነውና፤ ጎጂም አልኩት አንተን አለመልቀቁ ሱሰኛም ማድረጉ አንተ ላይ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ያመጣልና ነው። ሴጋና ልጆች ሴጋ ከሚያስከትለው ዘለቄታዊ አንዳንዴም(በወቅቱ ካልቆመ) የእድሜ ልክ ችግር ከመኾኑ አንጻር ልጆች ወደ ጉርምስና እድሜያቸው እየተቃረቡ ሲሄዱ ስለወሲብ ጸጋነትና አግባባዊ አጠቃቀሙ መማር አለባቸው። በተለይም አኹን ባለንበት ነባራዊ ዘመን የወንዶች ወንዳወንድነት ባሽቆለቆለበትና አባቶችም ወንዳወንድ ጠባይ በማያሳዩበት በዚህ ወቅት ልጆች በተለይም ሴቶች ልጆች ቶሎ ለመጎርመስና ለተሳሳተ የወሲብ ግንዛቤና ድርጊት ይጋለጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዘመን በወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤት በኾኑ መሣሪያዎች የምናገኛቸው የወሲብ ትዕይንቶች(Pornography) ችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ። ምንም እንኳ ሴጋ በአብዛኛው የወንዶች ክፉ ልማድ ቢኾንም ከወሲባዊው አብዮት ወዲህ ግን የሚለማመዱት ሴቶቹም ቁጥር ጨምሯል። አንተ ታዲያ ሚስትህንና ልጆችህን(ወንዱንም ኾነ ሴቷን) ስለወሲብና ትክክለኛ(አግባባዊ) አፈጻጸሙ፣ ስለሴጋም ጎጂነት ታስተምር ዘንድ አንተ መጀመሪያ አውቀኸው(ጉዳቱንም ጭምር) ራስህንም ጠብቀህ ልትገኝ ይገባል። በዚህም መሠረት ሚስትህም ኾነች ልጆችህ በዚህ ልማድ እንዳይገኙ ሥርዓትን ልትሠራላቸው፣ ልትመክራቸው ፈጽመውት ቢገኙ ደግሞ ልትቀጣቸው ይገባሃል። የሴጋ ጎጂ ልማድነት(ከወንዶቹ አንጻር) ጉዳት ፩ አካላዊ ጉዳት ውዱ ወንድሜ! ሴጋ በቋሚነት የምትመታ ከኾነ የሰውነትህን ፈሳሽ፣ ወዝህን፣ ጉልበትህን አሟጦ ይጨርሰዋል። ይኽም ማለት ከሴጋህ በኋላ ሰውነትህ ይልፈሰፈሳል፣ አይንህ ይፈዛል(ስብር ይላል)። "እንዴዬ ወሲብስ ከሚስቴ ጋር ስፈጽም ይደክመኝ የለ?" ብትለኝ አዎን ወሲብም ከሚስትህ ጋር ብትፈጽም ይደክምሃል። ነገር ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ሰውነትህን የማይመጥ ጉልበትህንም የማይጨርስ ይልቁንስ መታደስ ያለበት ነው። ይኽ የሚኾነው ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ሴጋህን የሚያስረሳ እርካታውም የጋራ መኾን ያለበት እንጂ ዝምብለህ እንደነገሩ ተንደፋድፈህ መነሳት ከኾነ ውጤቱ ከሴጋው ብዙም አይለይም። ጉዳት ፪ አእምሮአዊ ጉዳት በተለይም በዚህ ዘመን ለሴጋ ወሲባዊ ትዕይንቶች(Pornogra phy) ከፍተኛ መንሴዔዎች ናቸው። በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልናቸውን መልእክቶች ተንተርሶ አስፈላጊው አጸፋዊ ምላሽ በሚመለከተው የሰውነት ክፍል እንዲሰጥ የሚያዘው አእምሮ ነው። በወሲባዊ ትዕይንቶች የተነካው(መልእክት የተቀበለው) የአእመሮአችን ክፍል የልብ ምታችን እንዲጨምር፣ ደምም በፍጥነት እንዲዘዋወር (በተለይም ወደ ብልታችን) ከዚህም የተነሳ እንዲነቃቃ ያደርጋል። ይኽን ልማድ ያደረገው አእምሮህ ታዲያ ሚስትህን ስታይ፣ ጠረኗ ሲሸትህ፣ ሰውነቷን ስትዳብስ(ስትዳብስህ)፣ ለወሲብም ወደምንጣፍህ ስትወጣ አእምሮህ ሰውነትህን ለማዘዝ ይዘገያል(አያዘውም)። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ የሚያውቀውና የለመደው ስሜት መቀስቀሻ ሌሎች ወሲብ ሲፈጽሙ ማየት ነውና። ጉዳት ፫ ስነልቦናዊ ጉዳት ሴጋ ስትመታ "ወሲቡ"(ከተባለ) አንተ በራስህ ለራስህ ብቻ የምትፈጽመው የምትወዳትን ሚስትህን ያላሳተፈ ነውና በራስወዳድነት ማዕበል እየተንገላታህ ለሚስትህ ያለህ ናፍቆትና ስስትም እየቀነሰ ይሄዳል። አለባበሷን ማድነቅ፣ የናፍቆትና የፍቅር ቃላትን መናገር፣ ፈቃዷን መፈጸምና ፍላጎቷንም በአግባቡ ማርካት ይሳንሃል። ምክንያቱ ደግሞ የእነዚህ ምንጭ የኾነውን ወሲባዊ ስሜት (መነቃቃት) በሴጋ አድርቀኸዋልና ነው። ጉዳት ፬ ከሴት ያርቅሃል ሴጋን በቋሚነት ለሚመታ ወንድ ሴቶችን መቅረብ(መጥበስ)፣ ማናገር(መጀንጀን) ይሳነዋል። የመጠየቅ፣ የመነጋገርና የመግባባት ብሎም የመፋቀርን ሽልማትና እርካታ በዋዛ በሴጋ ያገኘዋልና(ምንም እንኳ ሴጋ ለወሲብ ምትክ ባይኾንም)። ጉዳት፭ ወኔህን ይሰልበዋል ፈርጀብዙ የኾነ አባወራዊ ሚናህን የምትወጣበትን ወኔ ይገድለዋል። እያደርም ለቤትህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ግድ የሌለህ በራስወዳድነት ባሕር ሰምጠህ እንድትቀርም ያደርግሃል። ጉዳት ፮ ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል ውድ ወንድሜ! እኔ ይኼን ስጽፍልህ ትማርበት ዘንድ በእርሱም ፈጣሪ የሰጠህን ጸጋ በአግባቡ ተጠቅመህ በትዳርህ አንድነትህን ታጠነክርበት ዘንድ ነው። እርግጠኛ ኾኜ የምነግርህ ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ነው። @yetedeberut
Aug 12, 2021